መደበኛ ብድር / Ordinary Loan

 • 3/ሶስት ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 120‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡

 • 4/አራት ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 200‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡

 • 5/አምስት ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 300‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡

 • 6/ስድስት ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 500‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡

 • 7/ሰባት ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 600‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡

 • 8/ስምንት ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 700‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡

 • 9/ ዘጠኝ ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 800‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡

 • 12/አስራ ሁለት ወር/

  በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 1‚000‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወራት ድረስ ይሆናል።

የመኪና ብድር<br>Car Loan

የመኪና ብድር
Car Loan

የመኪና ብደር 12 - 16/አስራ ሁለት ወር እስከ አሰራ ሰድስት ወር / በተከታታይ የሚበደረውን 20 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 10% እጣ የገዛ አባል የመኪና ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው ከ 1,500,000.00 እስከ 2‚000‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 120 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡
የቤት ብድር<br>Home Loan

የቤት ብድር
Home Loan

የቤት 16/አስራ ስድስት ወር/ በተከታታይ የሚበደረውን 15 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 10% እጣ የገዛ አባል የቤት ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 3‚000‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 120 ወራት ድረስ ይሆናል፡

ብድር ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

 • አጠቃላይ ለብድር መሟላት ያለባቸው ማስረጃወች

 • የብድር ጠያቂዉ የማኅበሩ አባል መሆን አለበት

 • አባል ሁኖ ሁለት ወራት መቆየት ይኖርበታል

 • እንደሚበደረው የገንዘብ መጠን በማኅበሩ የተቀመጠውን የቆይታ ጊዜ ማሟላት አለበት

 • በሚጠይቀው የገንዘብ መጠን ልክ በማኅበሩ የተቀመጠውን ሼር የገዛ እና ቁጠባውን ቀድሞ ወይም ሳይቆራረጥ

 • ብድሩን እስኪጠይቅ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የቆጠበ መሆን አለበት

 • የገቢ ማስረጃ እና ዋስትና ማቅረብ የሚችል

 • የታደሰ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ የሚችል

 • የተበዳሪውንም ሆነ የዋሱን ያገባ ያላገባ ጊዜው ያላለፈበት ሰርትፊኬት ማምጣት የሚችል

 • ለንግድ ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርትፊኬት እና የ1 ዓመት የቤት ኪራይ ውል

በብድሩ እና በዋስትናው አይነት

ዝርዝር መስፈርት

መደበኛ ብድር

መደበኛ ብድር የሚባለው ጣራው 1 ሚሊየን ብር ሁኖ አባሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዎ አገልግሎቶች የሚወስዳቸው ብድሮች ሲሆኑ የአባሉ መዋጮ 15% ይሆናል፡፡ ዋስትናቸው የተለያየ ሲሆን ከዋስትናው ጋር የተገናኙ መስፈርቶች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
 • 1. በደመወዝ ዋስትና የሚሰጥ ብድር

  • ከባንክ፣ ኢንሹራንስ ወይም መሰል ትልቅ ተቋማት የተገዙ ሸሮችን ወይም የሸገርን ሸርና ቁጠባ አባሉ እንደ ዋስትና ተጠቅሞ ብድር መውሰድ ይቻላል፡፡ የብድሩ መጠንም በሸሩ መጠን ልክ ይሆናል፡፡
  • ሼሩ ከተገዛበት ተቋም የእግድ ደብዳቤ ከመጣ በኋላ እና ተበዳሪው ከላይ የተቀመጡት አጠቃላይ ማስረጃዎች ከተሟሉ ብድሩን መውሰድ ይችላል፡፡
  • ዋስትናው የሸገር እጣ እና ቁጠባ ከሆነ በሼሩ እና ቁጠባው መጠን ልክ ብቻ ብድር መውሰድ ይችላል ነገር ግን ብድሩ ተከፍሎ እስከሚጠናቃ ድረስ ሼሩንም ሆነ ቁጠባውን ማውጣት አይችልም፡፡
 • 2. የተለያዩ ተቋማትን ሸር በዋስትና በመጠቀም የሚሰጥ ብድር

  • በደሞዝ ዋስትና ለፍጆታ የሚሰጥ ብድር ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር መብለጥ የለበትም፡፡
  • በደሞዝ ዋስትና ለንግድ፤ ለተጨማሪ የቤት እና የመኪና ግዥ ክፍያ ለመሙላት እና ለኮንዶሞኒየም ቅደመ ክፍያ ለመሙላት የሚሰጥ ብድር ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ)ብር መብለጥ የለበትም፡፡
  • የሚያቀርበው የተበዳሪም ሆነ የዋስ የዋስትና ደብዳቤ ከመንግስት መስሪያ ቤት እና ከታወቀ ድርጅት እና መ/ያ/ድ መሆን አለበት፡፡ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የደመወዙ መጠን፤ ቋሚ ሰራተኛ መሆኑንና ጡረታ ለመውጣት የቀራቸው ጊዜ፤ ከሌላ ተቋም ብድር የወሰደ መሆንና አለመሆኑን፣ ተበዳሪውም ሆነ ዋሱ መስራ ቤቱን ቢለቁ በቅድሚያ የሚያሳዉቁ መሆኑን እና የስራ ግብር ከፋይ መሆኑን የሚገልጽ እና የግል ድርጀት ከሆነ ድርጀቱ ከ10 ዓመት በላይ የቆየ እና ሰራተኛው የስድስት ወር ፔሮል ማስረጃ ማቅረብ አለበት፤ የዋሱ ሚስት/ባል መፈረም አለበት/ባት፡፡
 • 3. በመኪና/ቤት ዋስትና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሰጥ ብድር

  • የሚሰጠው ብድር መኪናው ኢንሹራንስ ከገመተው እና ከተገዛበት ዋጋ 85% በላይ መሆን የለበትም
  • በዋስትና የሚያዘው መኪና ከተመረተ/በሊብሬው መሰረት/ 20 አመት ያልበለጠው መሆን አለበት
  • መኪናው ተፈትሾ ለብድር ዋስትናው ብቁ መሆን አለበት
  • ቤቱ ለብድሩ ተመጣጣኝ ዋስትና ሊሆን ይገባላ
  • ቤቱ ካርታና ፕላን ሊኖረው ይገባል ግንባታውም በፕላኑ መሰረት መሰራት ይኖርበታል
  • ለቤቱ የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ያስፈልጋል
  • የመኪናው ሊብሬ ከታገደ እና ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩት አጠቃላይ መስፈርቶች ከተሟሉ በኋላ ብድሩ ይለቀቃል

የመኪና ብድር

 • አባሉ ለመኪና መግዣ የሚውል እስከ 2 ሚሊዮን ብር ብድር መውሰድ ይችላል ነገር ግን የመኪናው እድሜ ከ 20 አመት በታች መሆን ይኖርበታል፡፡

 • አባሉ የሚበደረውን ብድር 30% ከ1 አመት እስከ 1 አመት ከ6 ወር ጊዜ ውስጥ መቆጠብ እና ሼር መግዛት ከቻለ ብድሩን መጠየቅ ይችላል

 • መኪናውን እራሱ ተበዳሪው ይሆናል የሚገዛው ለሻጭ ለሚከፈለው ክፍያ የኛ መተማመኛ ደብዳቤ ይሰጣል፡፡

 • የመኪናው ምርመራ የኛ በፈለገው ተቋም ይካሄዳል የምርመራው ውጤት ብቁ ከሆነ እግድ ተያይዞ፣ ሙሉ ጣምራ ኢንሹራንስ በየኛ እና በተበዳሪው ተገብቶ እና ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩት አጠቃላይ መስፈርቶች ከተሟሉ በኋላ ብድሩ ይለቀቃል፡፡

የቤት ብድር

 • አባሉ ለቤት መግዣ የሚውል እስከ 3 ሚሊዮን ብር ብድር መውሰድ ይችላል

 • አባሉ የሚበደረውን ብድር 25 % 1አመት ከ 6 ወር ጊዜ ውስጥ መቆጠብ እና ሸር መግዛት ከቻለ ብድሩን መጠየቅ ይችላል

 • ቤቱን እራሱ ተበዳሪው ይሆናል የሚገዛው ለሻጭ ለሚከፈለው ክፍያ የኛ መተማመኛ ደብዳቤ ይሰጣል፡፡ ቤቱ ለብድሩ ተመጣጣኝ ዋስትና ሊሆን ይገባል

 • ቤቱ ካርታና ፕላን ሊኖረው ይገባል ግንባታውም በፕላኑ መሰረት መሰራት ይኖርበታል ለቤቱ የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ያስፈልጋል

 • ቤቱ በአካል ታይቶ ይሁንታ ካገኘ፣ እግድ ተያይዞ፣ ሙሉ ጣምራ ኢንሹራንስ በየኛ እና በተበዳሪው ተገብቶ እና ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩት አጠቃላይ መስፈርቶች ከተሟሉ በኋላ ብድሩ ይለቀቃል፡፡