ራዕይ
ጠንካራ የቁጠባ ባህልን በማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት እንዲሁም በኢኮኖሚ የበለጸገ ህብረተሰብን በመፍጠር፤ በ2027 በምስራቅ አፍሪካ ተቀዳሚ ፣ተመራጭ እና ተምሳሌት የሆነ የህብረት ስራ ማህበር መሆን
ተልዕኮ
በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ከአባላት የሚገኘውን ገንዘብ በቁጠባ መልክ በማሰባሰብ የገንዘብ ክምችት እንዲዳብር በማድረግ በጋራ ማደግን ፍላጎት ያደረገ የቁጠባ፣ ብድር እና ባንክ ነክ አገልግሎት በመስጠት የአባላትን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ለሃገራችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጾ ማድረግ
አላማ
የቁጠባ ባህልን በማሳደግ እና ለአባላት ምቹና አስተማማኝ የፋይናንስ አገልግሎቶችን መስጠት በባንክ ስርአት የፋይናንስ ፍላጎታቸውን ሊያሟሉ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን አገልግሎት መስጠት
አባል ለመሆን
-
በሕግ መብቱ ያልተገደበ
-
ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
-
የኅብረት ሥራ ማህበሩን የመተዳደሪያ ደንብ፣ መመሪያዎችና የአሠራር ደንቦችን የተቀበለና ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ
-
የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500፣ የዕጣ (ሼር) ዋጋ ብር 1,000
-
የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ / መንጃ ፍቃድ
-
ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
ብድር ለመውሰድ
-
የብድር ጠያቂዉ የማኅበሩ አባል መሆን አለበት
-
አባል ሁኖ ሁለት ወራት መቆየት ይኖርበታል
-
የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500፣ የዕጣ (ሼር) ዋጋ ብር 1,000
-
በሚጠይቀው የገንዘብ መጠን ልክ በማኅበሩ የተቀመጠውን ሼር የገዛ እና ቁጠባውን ቀድሞ ወይም ሳይቆራረጥ ብድሩን እስኪጠይቅ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የቆጠበ መሆን አለበት
-
የገቢ ማስረጃ እና ዋስትና ማቅረብ የሚችል
-
የታደሰ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ የሚችል
ሌሎች አገልግሎቶች
የስራ ማስኬጃ እቁብ ፣ የማማከር አገልግሎት ፣ አነስተኛ የመድህን ወይም ተካፉል አገልግሎት ፣ የባጃጅ መግዣ እቁብ ፣ የፎርስ መግዣ እቁብ ፣ የመኪና መግዣ እቁብ